የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ

ከ17 አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ22 አመታት የስርአቱን
ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ አፓርታይድ ስርአት
ተቀይሮዋል።
ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት 21 አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ
ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ።
ለመጥቀስ ያክል ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ የህወሐት ባላስልጣናት ትእዛዝ መለስን ጨምሮ
በጋምቤላ፣በኦሮሞ፣በአማራ፣በኦጋዴን እና በደቡብ ህዝቦች ላይ አስከፊ የእስራት የግርፋት እና የጅምላ ግድያ ወንጀል
ተፈፅሟል አሁንም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ዜጎችን በሀገሪቱዋ በየትኛዉም አካባቢ የመኖር የሀገሪቱዋ ህገ
መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ የዘር ማፅዳት ወንጀል በህወሐት አምባገነን መሪዎች እየተፈፀመ ነዉ።
በ፩፱፰፫፣፰፬ ጋምቤላ፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፮ በኦሮምያ ጅማ፣ሰጠማ፣ሲጊሞ እና ጌራ የሚባሉ አካቢዎች፣ከ፩፱፰፬ እስከ
፩፱፰፰ በአማራ ተወላጆች ላይ በበደኖ፣ወተር፣በአርሲ ባሌ፣በሐረር ጉርሱም አካባቢ፣ከ፩፱፱፱ እስከ ፪፲፻
በደግሐቡር፣በቀብሪደሐር እና በኦጋዴን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በመከላከያ ሠራዊት በጦር ሄሊኮፕተር በመታገዝ አሰቃቂ
የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል።ከወራትም በፊት በደቡብ ኦሞ እና በጋምቤላ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል
ተፈፅሟል። ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምና አሁንም እየተፈፀመ ባለበት ወቅት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ማንም ተከሶ ለፍርድ የቀረበ
የለም ነር ግን ይሄን ሁሉ በደል እና ግፍ የተቃወሙና የፃፋ ንፁሀን ያገሪቱ ዜጎች ለአፈና፣ለስደትና ለእስር ተዳርገዋል።
በስደት ያሉትን ባልዘረዝርም ሀገር ዉስጥ ሆነው በሀገሪቷ ህገመንግስት ተጠቅመው ስርዐቱን ስለተቃወሙና ስለፃፋ
ከእድሜ ልክ እስከ ረጅም አመት እስራት ተፈርዶባቸዉ በእስር ላይ ያሉና እስርቤትም ሆነው ይግባኝ በማለትም ሆነ
ባለማለት በሀገሪቷ የመጨረሻዉ ጠቅላይ ህወሐት ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን ያበሰሩንን ጀግኖች ጠቅሳለሁ፣
ሌልሴ ወዳጆ፣ርዮት አለሙ፣እስክንድር ነጋ፣በቀለ ገርባ፣አንዱአለም አራጌ፣ዉብእሼት ታዬ፣የድምፃችን ይሰማ
ኮሚቴዎች>>>ወዘተ ኮራንባችሁ ያላችሁበት ህይወት የኛ ሆኖ ቢያቃጥለንም።
በአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ላይ የይግባኝሽ ፍርድ ቤት ያፀናዉ ፍርድ ከመለስ ሞት በውሓላም ህወሐት ፍትህን የገደለ የአፓርታይድ ስርዐት
መሆኑን አሳውቆናል። ስለሆነም ከሰሜን ኮርያ በላይ የከፋው የህወህት ስርዐት ጋዜጠኛ ተመስገን
ደሳለኝን እየተደገሰለት ባለዉ የዉሸት ፖለቲካ ክስ እሱንም በይግባኝ ፍርድ ቤት ጭምር ከምናምን እድሜ እስር ጋር ቂሊንጦ ወይም ዝዋይ እስርቤት
ማየታችን አይቀርም። እናም የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቷ ፍትህ መቀበሩን አረጋግጦልናል።
ውድ አንባቢዎቼ ነገር ግን እኔም ተመስገን ደሳለኝ ነኝ እናንተስ? ሀገራችንን እና ህዝቧን ከአፓርታይድ ስርዐት ዛሬዉኑ እንታደግ!!!
ህዝብ ያሸንፋል።Image

Advertisements